ቀጥታ፡

የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ዛሬ ያደርጋል።

ለጨረታ የሚቀርበው የውጭ ምንዛሪ መጠን 60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ጨረታው ለሁሉም ባንኮች ክፍት እንደሚሆን ገልጿል።

ብሔራዊ ባንክ በቀጣይ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ይህም የባንኩን የዋጋና የውጭ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማስፈን ያስቀመጠው ስትራቴጂአዊ ግብ አካል እንደሆነም ተመላክቷል።

ባንኮች በተዘጋጀው ጨረታ ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም