ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከሯል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ ሳላህ እና ዶምኒክ ስቦዝላህ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል በ64 ነጥብ ከተከታዩ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 11 ከፍ አድርጓል።

ሊቨርፑሎች ከሌሎቹ የሊጉ ክለቦች የበለጠ አንድ ተጨማሪ ጨዋታ አድርገዋል።

የአምናው የሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ በ44 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ድንቅ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኘው የ32 ዓመቱ ግብጻዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች መሐመድ ሳላህ በሊጉ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛት ወደ 25 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን አስቆጥሯል።

በተጨማሪም ሳላህ በሊጉ 16 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም