ቀጥታ፡

አቶ አደም ፋራህ ለ8ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የተርኪዬ ኤኬ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ለ8ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የተርኪዬ ኤኬ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡


 

ከብልፅግና ፓርቲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ለመስራት በቅርቡ የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመው ኤኬ ፓርቲ በዛሬው እለት ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።


 

በዚህም የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ከፓርቲው በቀረበው የተሳትፎ ግብዣ መሰረት በጠቅላላ ጉባዔው ላይ መገኘታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም