ቀጥታ፡

ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የተማረ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው

መቱ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የተማረ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል ዲማ ኖጎ(ዶ/ር) ገለጹ።

መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 407 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።


 

በምርቃት መርሃ ግብሩ የተገኙት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል ዲማ ኖጎ(ዶ/ር) ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የተማረ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲዎች ብቁ የሰው ሀይል የማፍራት ተልዕኳቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ዓለሙ ዲሳሳ(ዶ/ር) በበኩላቸው ምሩቃን ሀገርና ህዝብን ተጠቃሚ ለሚያደርጉ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው በኃላፊነት እንዲንቀሳቀሱ አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ካስመረቃቸው ምሩቃን መካከል 226ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታታሉ የቆዩ መሆናቸውም ተገልጿል።

መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ የዛሬው ለ12ኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም