በሸገር ከተማ የሕዝብ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
በሸገር ከተማ የሕዝብ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በሸገር ከተማ የሕዝብ ኮንፍረንስ መካሄድ ጀምሯል።
ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፍረንስ ከዛሬ ጀምሮ በ25 የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች እንደሚካሄድ ብልፅግና ፓርቲ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
በኮንፍረንሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)፣ በሸገር ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አለማየሁ ቱሉ እና የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ኃላፊ መሠረት አሰፋ ተገኝተዋል።
በሕዝብ ኮንፍረንሱ ላይ ከከተማዋ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።