ቀጥታ፡

ሉሲዎች በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዩጋንዳ ተሸነፉ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በ16ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ከዩጋንዳ ጋር ባደረገው የማጣሪያ ጨዋታ በዩጋንዳ አቻው 2 ለ 0 ተሸንፏል።

በካምፓላ ሀምዝ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናዚያህ ናሙሌሜ በ90ኛው እና ፋዚላ ኢክዋፑት በ93ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ የሚመራው ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አበ ቢቂላ ስታዲየም ያደርጋል።

ቡድኑ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ተጋጣሚውን ከሁለት ግብ በላይ ልዩነት ማሸነፍ ይኖርበታል። 

ሉሲዎቹ በደርሶ መልስ ዩጋንዳን ካሸነፉ በሁለተኛው ዙር ከታንዛንያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ። 

እ.አ.አ በ2026 በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ 12 ሀገራት ይሳተፋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም