የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሀፊ ጊልስ ሚቻውድን ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።
ኮሚሽነር ጀነራሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚያከናውናቸው ተልዕኮዎች እንዲሳኩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እየተወጣ ያለውን ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሀፊ ሚስተር ጊልስ ሚቻውድ የኢትዮጵያ ፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስምሪትንም ለማስፋት ላቀረበው ጥያቄ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።