የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአመቱ ምርጥ "የአፍሪካ የጭነት አየር መንገድ'' ሽልማትን አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአመቱ ምርጥ "የአፍሪካ የጭነት አየር መንገድ'' ሽልማትን አገኘ
አዲስ አበባ፤የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአመቱ ምርጥ "የአፍሪካ የጭነት አየር መንገድ'' ሽልማትን አግኝቷል።
ናይሮቢ በተካሄደው የስታት ታይምስ ኢንተርናሽናል የአየር ካርጎ ልህቀት ሽልማት፥ በአመቱ ፋጣን እድገት ያስመዘገበ አየር መንገድ እና ምርጥ አለም አቀፍ የጭነት አየር መንገድ ተብሎም እውቅናን አግኝቷል።
አየር መንገዱ ለዚህ ስኬት የበቃው በላቀ ደረጃ አገልግሎቱን በመስጠት፥ በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ጭነት(ካርጎ) ሎጂስቲክስን በማስፋፋት መሆኑን ገልጿል።