በአምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልዑካን ቡድን ኩዌት ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በአምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልዑካን ቡድን ኩዌት ገባ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፦በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሚገኙበት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኩዌት ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ ኩዌት አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሀመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃነስ አል ኦይታይቢ፣ ዲፕሎማቶች፣ በኩዌት የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አመራሮችና ዳያስፖራዎች አቀባበል አድርገውለታል።
የልዑካን ቡድኑ በቆይታው በ129ኛው የአድዋ ድል በዓል እንዲሁም በኩዌት የኢትዮጵያ ቀን በዓል እንደሚታደም በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ከዳያስፖራ አባላት ተወካዮች ጋር የውይይት መድረክ እንደሚያደርግ እና የኢትዮጵያውያንን የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚጎበኝም ተገልጿል።