ኢትዮጵያ እና ህንድ ወዳጅነት እና አጋርነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ህንድ ወዳጅነት እና አጋርነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተስማሙ
አዲስ አበባ፣የካቲት 13/2017( (ኢዜአ) :ኢትዮጵያ እና ህንድ ወዳጅነት እና አጋርነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተስማምተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግ በመካሄድ ላይ ካለው የቡድን 20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መድረክ ጎን ለጎን ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄይሻንካር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት የህንዱ አቻቸው ጄይሻንካር ጌዲዮን (ዶ/ር ) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው "እንኳን ደስ አለዎት" ብለዋቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት እና አጋርነት ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተስማምተዋል።