ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በቡድን 20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ ፤ የካቲት 13/ 2017 (ኢዜአ )፦በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር ) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በቡድን 20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ በመሳተፍ ላይ ነው።

ጉባኤው “አንድነት፣ እኩልነት እና ዘላቂነት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን  የውይይት መድረኩም በደቡብ አፍሪካው  ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በይፋ ተከፍቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር አለም በጂኦፖለቲካል ውጥረቶች፣ ግጭቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት  በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እየገባች ነው ብለዋል። 

ሚኒስትሩ በፉክክር እና በትብብር መካከል ትክክለኛ ሚዛን ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው የቡድን 2ዐ አባል ሀገራትን ጨምሮ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ መካከል የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ አረጋግጠዋል።
 
ለሁለት ቀናት የሚዘልቀው ይህ ጉባኤ  በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ሰላም እና ፀጥታ፣ ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ አስፈላጊነት እና የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅእኖዎችን ለመከላከል የሚወሰዱ የጋራ ዕርምጃዎች እና ሌሎችንም ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም