ሰባተኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህል እና "ዋዛ" ፌስቲቫል በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሰባተኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህል እና "ዋዛ" ፌስቲቫል በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው
አሶሳ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ):- ሰባተኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህል እና "ዋዛ" ባህላዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሳሪያ ፌስቲቫል በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በፌስቲቫሉ ዋዛን በዓለም ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ያለመ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ እንደሚመከርበት ይጠበቃል።
በተጨማሪም የዐውደ ርዕይ እና ባዛር እንዲሁም ባህላዊ ጭፈራዎች ይካሄዳሉ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነጥበብና ስነ-ጥበብ ፈጠራ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ነፊሳ አልማሃዲ እና የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩርን ጨምሮ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተዋል።
እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ መለሰ ኪዊ እና ሌሎች ተሳታፊዎችም ተገኝተዋል።