ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የስራ ኃላፊዎችን ሹመት አጸቀደ

ወልቂጤ፤የካቲት 13/2017 (ኢዜአ) :-የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የቀረበለትን የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የስራ ኃላፊዎችን ሹመት ተቀብሎ አፅድቋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀረበለትን የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ሹመቶችን ተቀብሎ አፅድቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-

1. አቶ አሊ ከድር፡- የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

2.አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፡- የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ

3.አቶ አሰፋ ደቼ ፡- የክልሉ ቴክኒክና ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ

4.ወይዘሮ ዘቢባ መሀመድ ናስር፡- የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

5.አቶ ሳሙኤል ዳርጌ፡- የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ

6.አቶ አብርሃም መጫ፡- የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ

7.አቶ ዘሪሁን እሸቱ ፡- የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

8. አቶ ጌታቸው ሌሊሾ፡-የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል።

ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም