ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከእንግሊዝ መንግሥት የ12 አምቡላንሶች ድጋፍ ተረከበ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በኢትዮጵያ የሚገኙት የእንግሊዟ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር በሀገሪቱ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት የተገዙ 12 አምቡላንሶችን ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስረክበዋል።

አምቡላንሶቹን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ተረክበዋል።

May be an image of ‎9 people, lumberyard and ‎text that says '‎S ا +‎'‎‎

አምቡላንሶቹ ለእናቶችና ህፃናት አስቸኳይ ሰብዓዊ አገልግሎት የሚውሉ የህክምና ግብዓቶችን ያሟሉ መሆናቸውም ተመላክቷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሰብዓዊ ተግባራትን የጎበኙ ሲሆን ከማኅበሩ አመራሮች በትብብር በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

May be an image of ambulance, hospital and text that says 'R Ethiopia Crises to Resilience សា្អាមា្ា 가이 REACH more elfective Intores action WFP British Red Cross World Food Programme unicef for every child CASOs CROSS Handing Over of Well-Equipped Ambulances Save Lives and Reduce Suffering in Conflict-and Drought-Affected Hard-to-Reach Areas ated by: 米 February, 2025 ukaid from ป Briteh people We Live for Human'

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም