ቀጥታ፡

አርሜንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር ትሻለች

አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ አርሜንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ለማስፋት ፍላጎት እንዳላት በኢትዮጵያ የአርሜንያ አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን ገለጹ።

አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን ለኢዜአ እንዳሉት የኢትዮ-አርሜንያ 30 ዓመታት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

አርሜንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ለማስፋት ፍላጎት እንዳላት አምባሳደሩ አስታውቀዋል።

አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች የመግባቢያ ስምምነቶች መፈራረማቸውን አስታውሰው በቀጣይም የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚያጠናክሩ ስምምነቶች እንደሚኖሩ ገልጸዋል።

ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የትብብር አቅምን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በተለይም ሴቶችን ጨምሮ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከመደገፍ አኳያ በጋራ እየሰሩበት መሆኑን አመላክተዋል።

የትምህርት ዘርፍ መንግስታቸው ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር መስራት ከሚፈልግባቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም የታዳጊዎችን ፈጠራና ክህሎት የሚያሳድጉ የትምህርት ማዕከሎችን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም