ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከራሺያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከራሺያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ እና ከልዑክ ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ምሽት ከራሺያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተገናኝተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ እና የራሺያ ግንኙነቶችን ለመዳሰስ እና ለመወያየት ጥሩ እድል ፈጥሮልናል ሲሉም ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም