የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቫለንቲና ማትቪየንኮ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
አፈ ጉባዔዋ ማትቪየንኮና ልዑካቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አገኘሁ ተሻገር አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑኩ ለሁለት ቀናት በሚኖረው የኢትዮጵያ ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይትና ጉብኝት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።