የኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ ማራካሽ በተጀመረው 4ኛው የአለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ እየተሳተፈ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ ማራካሽ በተጀመረው 4ኛው የአለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ እየተሳተፈ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ ማራካሽ በተጀመረው 4ኛው የአለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ Commit to life በሚል መሪ ቃል በሞሮኮ ማራካሽ በተጀመረው 4ኛው የአለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ የኢትዮጵያ ልዑካንን በመምራት እየተሳተፍን እንገኛለን ብለዋል።
ኮንፍረንሱ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚቆይም አስታውቀዋል።
ይህ ኮንፍረንስ በአለም ሀገራት በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ያሉ ቁልፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የትራፊክ አደጋዎችንና ጉዳቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እንዲሁም ቃልኪዳኖችን ይበልጥ ለማጠናከር ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉም ገልጸዋል፡፡