ቀጥታ፡

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ፖሊሲ ልማት ማዕከል ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ፖሊሲ ልማት ማዕከል ሃላፊ ሞኒካ ዛኔቴ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በስደተኞች ጉዳይ ያላቸውን የጋራ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተመሳሳይ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ፖሊሲ ልማት ማዕከል የኢትዮጵያ ቢሮውን መከፈት በሚችልበት ሁኔታ መነጋገራቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም