የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለተጨማሪ 1 ዓመት ተራዘመ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለተጨማሪ 1 ዓመት ተራዘመ
አዲስ አበባ፤የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀምን ከገመገመ በኋላ ለተጨማሪ 1 ዓመት እንዲራዘም ወስኗል።
ኮሚሽኑ በ2014 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሶስት ዓመታት በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ የተሳታፊ ልየታ እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራዎች ሲያከናውን ቆይቷል።
የኮሚሽኑ የስራ ዘመን ሊጠናቀቅ 3 ቀናት የቀሩት በመሆኑ ለተጨማሪ 1 ዓመት እንዲራዘም ምክር ቤቱ ወስኗል።
በምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ ኮሚሽኑን የሥራ ጊዜ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል።
ኮሚሽኑ የቀሪውን ሥራዎች ለማጠናቅ እንዲያስችለው አንድ ተጨማሪ ዓመት ተጨምሮለታል።
በዚህም የምክርቤቱ አባላት በውሳኔ ሀሳቡ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ከቀረቡ በኋላ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።