በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተሳተፉ የተለያዩ አገራት መሪዎች ወደ አገራቸው ተመለሱ - ኢዜአ አማርኛ
በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተሳተፉ የተለያዩ አገራት መሪዎች ወደ አገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፤የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ እና የቆይታ ጊዜያቸውን ያራዘሙት የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ እና የካሜሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ጀን ጉቴ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ለመሪዎቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የክብር አሸኛኘት ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።