ቀጥታ፡

በአፍሪካ የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር የአባል ሃገራት ትብብር ሊጠናከር ይገባል

አዲስ አበባ፤የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦በአፍሪካ የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር የአባል ሃገራት ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል።

በአፍሪካ ቲቢን የመቆጣጠር ኔትወርክ አመታዊ የውይይት መድረክ በአዲስ አበበ እየተደረገ ነው።

የአባል ሀገራት ትብብርን በማጠናከር ቲቢን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 22 የደቡብ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በውይይቱ ላይ የተካፈሉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ቲቢን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ምርምሮችን ለመስራት እያጋጠመ ያለውን የበጀት እጥረት ለመቅረፍ አባል ሀገራትም ሀገር በቀል የሀብት ማሰባሰብ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በውይይቱ ላይ የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ፣ምርጥ ተሞክሮ እንዲቀመር፣ ድንበር ዘለል ትብብር እንዲጠናከርና የጥምረቱ አካሄድ ሊገመገም እንደሚገባ መናገራቸውን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም