ቀጥታ፡

የኢትዮጵያና የዩናይትድ ኪንግደም ትብብር እያደገ መጥቷል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያና በዩናይትድ ኪንግደም መካከል ያለው ትብብር እያደገ መጥቷል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከዩናይትድ ኪንግደም አቻቸው አንጄላ ሬይነር ጋር በመሆን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

May be an image of 5 people, newsroom and text that says '0 ያኢርቲፈሻልኢንተለኛስ አርቲፊሻል አርቲፊሻ ኢንተለጀንስ የኢትዮጵያ የኢ PRETIS ትዮጵያ ኢንስቲን ETHIOPIANARTIF ARTIF ARTIF ETHIOPIAN GENO GENC'

የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጉብኝትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ትብብር እያደገ ስለመምጣቱ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ በቴክኖሎጂ እና በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም እንዲሁ።

ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም አያሌ ዓመታትን የተሻገር ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት እንደሆኑም ጠቅሰዋል።

May be an image of 6 people and dais

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም