በደቡብ ኦሞ ዞን በ132 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ የፀሐይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ኦሞ ዞን በ132 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ የፀሐይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ
ካራ ዱስ፤ የካቲት 10/2017 ዓ.ም(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በ132 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ ሁለት የፀሐይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
በምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ክንፈ ነጋሽ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂር አክሊሉ አዳኝን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ "ካራ-ዱስ" እና "ካራ-ቆርጬ" በተባሉ ቀበሌዎች የተገነቡት ፕሮጀክቶቹ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከኢትዮጵያ መንግስት በተገኘ 132 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን 450 አባውራዎችንም ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።
በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ የተገነቡት የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ 425 ኪሎ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸውም ተገልጿል።