ቀጥታ፡

በአፍሪካ ኀብረት ጉባኤ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፡- በ38ኛው የኀብረቱ አመታዊ የመሪዎች ጉባኤ የተካፈሉ መሪዎች እና የመንግስታት ተወካዮች ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ማያር ዴት፣ የሴኔጋል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ፣ የማዳጋስካር ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አንድሬ ራጆሊና፣ የዚምባቡዌ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤምርሰን ምናንጋግዋ እና የጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ሙባሎ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ገልጿል።


 

ለመሪዎቹ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል፣የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ(ዶ/ር)፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት የክብር አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም