ቀጥታ፡

በአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፡- በ38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀምረዋል።

በዚህም የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ተቡን፣ የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ፣ የፍልስጤም ፕሬዝዳንት መሐሙድ አባስ፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሊ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁድዝ ሲሙሟ በአዲስ አበባ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገሮቻቸው ተመልሰዋል።


 

ለመሪዎቹ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) እንዲሁም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው የክብር አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም