ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2017(ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ቀጣይነት ያለው ልማት ማዕከል ዳይሬክተር እና በተባበሩት መንግስታት ቀጣይነት ያለው የልማት ትስስር ፕሬዚደንት ከሆኑት ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በተለያዩ የልማት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውንና ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሆነው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።