ቀጥታ፡

አህጉራዊ የፋይናንስ ውህደትን ለማሳደግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣የካቲት 9/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያና የርዋንዳው ስቶክ ኤክስቼንጅ አህጉራዊ የፋይናንስ ውህደትን ለማሳደግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማዔል (ዶ/ር) እና የሩዋንዳ ስቶክ ኤክስቸንጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒየር ሴሌስቲን ራባቡኩምባ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ትብብርን ለማጎልበት፣ እውቀትን ለመለዋወጥ እና አህጉራዊ የፋይናንስ ውህደትን ለማሳደግ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

የተቋማቱ ስልታዊ አጋርነት የገበያ ልማትን ለማጎልበት፣ የአቅም ግንባታን ለማሳደግ እና በሁለቱ ገበያዎች አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የርዋንዳ ስቶክ ኤክስቼንጅን የካበተ ልምድ በመጠቀም በሁለቱ ሀገራት ያሉ የካፒታል ገበያዎችን ውሕደት እንደሚያጠናክር ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም