መንግስት ዛሬ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ለተመረጡት መሀሙድ የሱፍ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8 /2017 ( ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መንግስት በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ለተመረጡት የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀሙድ ዮሱፍ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል፡፡

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ"የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው ከሰአት በነበረው የመሪዎቹ ጉባኤ አጀንዳ አንዱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ይገኝበታል።

በምርጫው የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብበር ሚኒስትር ማህሙድ አሊ የሱፍ የ33 አባል አገራት ድምጽ በማግኘት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም