ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአፍሪካ የግል ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ከሆኑ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8/2017 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ የግሉ ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ከሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ እና ቶኒ ኢሉሜሉ ጋር ተወያዩ።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት ከአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ የግሉ ዘርፍ መሪ ከሆኑት ባለሀብቶች ጋር ተወያይተዋል።

ባለሀብቶቹ የአፍሪካ ዕድገት እውን እንዲሆን ወሳኝ ድርሻ እየተጫወቱ ስለመሆኑም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም