የኢንቨስትመንት አስፈፃሚዎች የጋራ የምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢንቨስትመንት አስፈፃሚዎች የጋራ የምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው
ጅግጅጋ ፤ የካቲት 8/2017 (ኢዜአ)፡- የፌዴራል ፣የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የኢንቨስትመንት አስፈፃሚዎች የምክክር መድረክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በዚህም የፌዴራል፣ የክልል እና ከተማ አስተዳድሮች የግማሽ በጀት ዓመቱ የስራ አፈጻጸም እንደሚገመግም ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
በተለይም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እያከናወነ የሚገኘውን መጠነ ሰፊ ስራዎች ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ እና ዘርፉ በሀገራዊ ዕድገት ላይ የራሱን አበርክቶ በማከል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግም ላይ ምክክር እንደሚካሄድ ተመልክቷል።
ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሸነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማንን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የኢንቨትመንትና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።