በጂንካ ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

ጂንካ የካቲት፤ 8/2017(ኢዜአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ቅዳሜ ገበያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ ገለጸ።

የአሪ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሽብሩ አማረ ለኢዜአ እንዳሉት በከተማዋ ቅዳሜ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ንጋት 11:30 ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱን ገልጸዋል።

አደጋው እንደተከሰተ የጂንካ አየር ማረፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ፖሊስና ነዋሪዎች ባደረጉት ርብርብ እሳቱን መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።

በሰው ህይወት ላይ ግን የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ኢንስፔክተር ሽብሩ ገልጸዋል።

የእሳት አደጋው የተከሰተበት ገበያ የሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች በጥግግት ያሉ በመሆናቸው የጉዳቱ ሰለባ መኖናቸውን ጠቅሰዋል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እና በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን በቀጣይ ምርመራና ማጣራት የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም