ሚኒስቴሩ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩን በቡታጅራ ከተማ እያካሄደ ነው

ቡታጅራ፣ የካቲት 7/2017 (ኢዜአ)፡-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር  ሚኒስቴር  የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን የሚገመግም መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

"በጥራት ወደ ተሳለጠ የንግድ ስርዓት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የንግድና ቀጣናዊ  ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የንግድ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤው የሚኒስቴሩ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫም እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

በተጨማሪም የሁሉም ክልሎች የሴክተር ቢሮዎች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የሚገመገም ሲሆን የንግድ ተቋማት የሥራ እንቅስቃሴ ላይም ምልከታ ይደረጋል።   

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም