የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፦ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሌ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊን ተቀብለው የዓድዋ ድል መታሰቢያን አስጎብኝተዋል።
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሌ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን የዓድዋ ድል የአንድነትና የጽናት ተምሳሌት እንዲሁም በትብብር ማንኛውንም ሃይል የማሸነፍ ምልክት መሆኑን መናገራቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ በዓድዋ ጀግኖች ሐውልት ስርም የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።