የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ ከሶማሊያው አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሀመድ ኦማር ጋር ውይይት አድርገዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዎች የተወያዩት ከ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው።


 

በውይይታቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከአንካራው ስምምነት መፈረም ወዲህ መሻሻሎች እያሳየ የመጣ መሆኑን አንስተዋል።

ግንኙነቱን በሌሎች መስኮች ማለትም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ለማስፋት የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ የማድረግ አስፈላጊነት ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም