ቀጥታ፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ን ለቀጣይ ሶስት ወራት ከምንም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማገዱን ገለፀ።

ሕወሓት ባለፈው ወርሃ ነሐሴ የምዝገባ እና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ተሰጥቶት እንደነበር ቦርዱ ባወጣው መግለጫ አስታውሷል።

ፓርቲው ባለፉት ስድስት ወራት ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጎ የፓርቲው አመራሮችን የማስመረጥ እና ጠቅላላ ጉባኤውን ከማድረጉ አስቀድሞ ለምርጫ ቦርድ ማሳወቅ ቢጠበቅበትም የተቀመጡ ሕጋዊ ድንጋጌዎችን እንዳልፈጸመ ገልጿል።

በዚህም ፓርቲው ለሶስት ወራት ምንም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ማገዱን ነው ያስታወቀው።

ፓርቲው በተሰጠው በሶስት ወራት ውስጥ የእርምት እርምጃ ካልወሰደ የፓርቲው ምዝገባ እንዲሰረዝ ቦርዱ መወሰኑን በተከታዩ ደብዳቤ አሳውቋል።

 


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም