ዓለም አቀፉ የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ እየተካሔደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ዓለም አቀፉ የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ እየተካሔደ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሀገራት የቀድሞ መሪዎች፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች ታድመዋል።
በመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር የተዘጋጀው ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።
በጉባኤው በመስኖ ልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መከላከል ዙሪያ ዓለም አቀፍ ልምዶችና ተሞክሮዎች ይቀርባሉ ተብሏል።
ጉባኤው የአየር ንብረት ተለዋዋጭነትን በመቋቋም የተሻሻለ የኑሮ ዘይቤ እና የመስኖ ልማትን ለማጎልበት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑም ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸው ተግባራት በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማትናአረንጓዴ አሻራ ዙሪያ ያላትን ልምድ እንደምታጋራም ይጠበቃል።
በጉባኤው የመስኖ ስራዎችን የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፍቷል።