ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት ትሰራለች- አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት ትሰራለች- አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ገለጹ።
አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የፕሮቶኮል ተጠባባቂ ሹም አቢ ጆንስ አቅርበዋል።
አምባሳደር ብናልፍ ከአቢ ጆንስ ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደሩ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
አቢ ጆንስ አምባሳደሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሚያከናውኑት ተግባራት አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።