ቀጥታ፡

የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሃመድ አሊ ዩሱፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሃመድ አሊ ዩሱፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አዚዛ ገለታ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 እንዲሁም 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ሁለንተናዊ ዝግጅት መደረጉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

በጉባዔው ከ15 ሺህ በላይ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም