ምክር ቤቱ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከየካቲት 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ያካሂዳል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከየካቲት 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ያካሂዳል

አርባምንጭ ፤ የካቲት 04/2017 (ኢዜአ) :- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከየካቲት 7 /2017 ዓ.ም ጀምሮ በአርባምንጭ ከተማ እንደሚካሄድ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ፀሐይ ወራሳ አስታወቁ።
አፈ-ጉባኤዋ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ጉባኤው የ3ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ በማጽደቅ የክልሉን መንግስት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ይገመግማል።
ምክር ቤቱም በኢንቨስትመንት፣ በግብርና ኮሌጅ ማቋቋሚያ፣ በከተሞች ደረጃ ማሻሻያና በበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ያተኮሩ አዋጆችንና የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ የሚጠበቅ መሆኑንም ገልጸዋል።
ጉባኤው ከየካቲት 7 እስከ 09/2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ፀሐይ ወራሳ አስታውቀዋል።