የሊቢያና የቱኒዚያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 03/2017(ኢዜአ)፦ የሊቢያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኢልታሄር ኢልቦር እና የቱኒዚያ የውጪ ጉዳዮች፣ የስደትና በውጪ የሚኖሩ ቱኒዝያዊያን ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ አሊ ናፍቲ ለአፍሪካ ሕብረት አባል አገራት የስራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ አዲስ አበባ ገቡ።

እንግዶቹ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አዚዛ ገለታ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም