የቤኒን፣ የካሜሮን፣ የናሚቢያና የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የቤኒን፣ የካሜሮን፣ የናሚቢያና የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፦ በ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።
በዚህም የቤኒን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አኮቪ ፊፋኒዴ ማርቲኔን አሞር ማሬ፣ የናሚቢያ አለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ፒያ ሙሼሌንጋ፣ የካሜሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጁኔ ምቤላ ምቤላ እና የቦትስዋና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር ፌኒዮ ቡታሌ ገብተዋል።
በተመሳሳይ የሌሴቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊኦኔ ምፖጇኔን እና የጀቡቲ የንግድ ሚኒስትር መሐመድ ዋርሳማ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖና የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለእንግዶቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።