ቀጥታ፡

ግዳጁ በምንም ሳይገደብ በላቀ ደረጃ መፈፀም የሚችል ሀይል ተገንብቷል - ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፦ማንኛውንም ግዳጅ በየትኛውም ቦታ እና የአየር ፀባይ መፈፀም የሚችል የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር መገንባቱን የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገለፁ፡፡

አዛዡ ስልጠናቸውን ያገባደዱ የልዩ ሀይል አባላትን በማነጋገር ስታር ዊንግ ደረጃ ለደረሱት የአየር ወለድ አሰልጣኞች ባለኮከብ ክንፍ አልብሰዋል።


 

በዚህ ወቅት ልዩና ወስብስብ ስልጠና ወስደው የተዘጋጁት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት የሀገሪቷ የመጨረሻ ሀይል በመሆናቸው ብዙ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

በግልም ሆነ በቡድን የትኛውንም ፈተና በማለፍ የሚሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመፈፀም መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።


 

ከጠላት ጀርባ ግራና ቀኝ ከአየር በመውረድ የጠላትን ስበት ማዕከል በመደምሰስ ሌላኛውን የሠራዊት ክፍል ለድል ማብቃት እንዲሁም በሀገር ውስጥ ይሁን ከሀገር ውጭ ህዝብንና ሀገርን የሚያሸብር ማስተር ማይንድ መምታት ከዚህ ክፍል ግዳጆች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል።

ሌተናል ጄኔራል ሹማ ክፍሉም ይህንን አቅም በላቀ ደረጃ እንዲኖረው ተደርጎ ስለመገንባቱ ማብራራታቸውን  ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም