አየር መንገዱ ወደ ሕንድ ሀይድራባድ ከተማ በረራ ሊጀምር ነው - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ ወደ ሕንድ ሀይድራባድ ከተማ በረራ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሕንድ 5ኛ የመንገደኛ በረራ መዳረሻ ወደምትሆነው ሀይድራባድ ከተማ አዲስ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ከሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሀይድራባድ ከተማ በሣምንት ሦስት ቀን የሚደረግ አዲስ በረራ እንደሚጀምር ነው የገለጸው።
የዚህ በረራ መጀመር አየር መንገዱ በሕንድ የሚኖረውን የበረራ አድማስ ከማስፋቱም በተጨማሪ በአፍሪካ እና እስያ መካከል ያለውን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።