የአዲስ አበባ ፖሊስን በሰው ሃይል ፣በቴክኖሎጂና በሎጂስቲክ የማጠናከር ውጤታማ ስራ ተሰርቷል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2017(ኢዜአ)፦ለውጡን ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስን በሰው ሃይል ፣ በቴክኖሎጂና በሎጀስቲክ ለማጠናከር ውጤታማ ስራ መሰራቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተናገሩ።

ኮሚሽነሩ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአባላቱንና የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት በማለም ያከናወናቸውን የልማት ፕሮጀክቶች መርቀው ስራ አስጀምረዋል ።

May be an image of 3 people, television and text

በሰው ተኮር የልማት ስራ ተመርቀው አገልግሎት መስጠት የጀመሩት የእንጀራ መጋገሪያና የዶሮ እርባታ ማዕከል ናቸው ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በጸጥታና ደህንነት ተቋማት በርካታ የሪፎርም ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከዚህ አንጻር የአዲስ አበባ ፖሊስ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሃይልና በመሰረታዊ ዘርፎች ውጤታማ የሪፎርም ተግባር ማከናወኑን ተናግረዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሃይል አደረጃጀትና በወንጀል መከላከል አመርቂ ስራ ማከናወኑን አስታውቀዋል።

መምሪያው ባለሃብቶችንና ህብረተሰቡን በማስተባበር የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማከናወን የሰራዊቱን ኑሮ ከመደገፍ ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ እገዛ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

May be an image of 6 people and text

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር መስፍን ሰብስቤ በበኩላቸው መምሪያው የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ውጤታማ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ኮሚሽኑ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በማከናወንና ምርት በማቅረብ የሰራዊቱን ህይወት እያሻሻለ ይገኛል ብለዋል።

የውስጥና የውጭ አቅምን በማስተባበር ሰራዊቱና ህብረተሰቡ የሚጠቀሙበትን ፕሮጀክት በፍጥነትና በጥራት አጠናቆ ማስመረቁን ተናግረዋል፡።

በመድረኩ ለልማት ስራው አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለሃብቶችና ድርጅቶች እንዲሁም ለፖሊስ አመራርና አባላት እውቅና ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም