ቀጥታ፡

የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ በነገው ዕለት በአዳማ ጨፌ አዳራሽ ይጀመራል



አዲስ አበባ፤የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፦የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 6ኛ የስራ ዘመን 8 መደበኛ ጉባኤ በነገው ዕለት በአዳማ ጨፌ አዳራሽ ይጀመራል።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን፥ ጉባኤውን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። 

በመግለጫቸውም፥ ጨፌ ኦሮሚያ የወከለውን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በጉባኤው በክልሉ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል በሚያስችሉ እና ተግዳሮችን መፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ብለዋል።

የህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ተፈትሸው አቅጣጫ የሚሰጥበት ጉባኤ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

ጨፌው የክልሉን የስራ አስፈፃሚ አካል የስድስት ወራት ክንውን በመገምገም፣ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡም ገልጸዋል።

ጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም