የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሀገር ውለታ የዋሉ ጀግኖች ቋሚ መታሰቢያ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሀገር ውለታ የዋሉ ጀግኖች ቋሚ መታሰቢያ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሀገር ውለታ የዋሉ ጀግኖች ቋሚ መታሰቢያ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ዛሬ የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኙ የኮማንዶና አየር ወለድ እዝ የሰራዊት አመራሮችን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ከሻለቃ በላይ ያሉ የሰራዊት አመራሮቹ በጉብኝቱ መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ በበኩላቸው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ምንም አይነት ልዩነት ቢኖር በሀገር ጉዳይ በጋራ በመቆም ፈተናዎችን የማለፍ ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ የሰራዊት አመራሮችና ሰራዊቱ ለሀገር እየከፈሉት ላለው ውድ ዋጋ ምስጋናቸውን አቅርበው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሀገር ውለታ የዋሉ ጀግኖች ቋሚ መታሰቢያ መሆኑን መግለጻቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።