ቀጥታ፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በጎንደር ከተማ የልማት ፕሮጀክቶችን ይመለከታሉ

ጎንደር ፤ጥር 29/2017 (ኢዜአ)፡- የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር  ጫልቱ ሳኒ በጎንደር ከተማ  የልማት ፕሮጀክቶችን  ይመለከታሉ ።

ሚኒስትሯ በፌደራል መንግስትና በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የመንገድና የኮሪደር ልማት መሠረተ ልማቶችን  ለመመልከት ጎንደር   ተገኝተዋል።

 በፌደራል መንግስት የበጀት ድጋፍ በከተማው የተጀመረው የአዘዞ ጎንደር የኮንክሪት አስፓልት ግንባታ ስራን የአፈጻጸም ደረጃን በመስክ እንደሚመለከቱ ተመላክቷል ።

 በመጀመሪያው ምእራፍ ተከናውኖ ለአገልግሎት የበቃውን የፒያሳ የኮሪደር ልማት ጨምሮ እስከ አዘዞ አየር  ማረፊያ የሚዘልቀውን 12 ኪሎ ሜትር  የሁለተኛው ምእራፍ የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴንም እንደሚመለከቱ ተገልጿል።

የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ስራም የምልከታው አካል መሆናቸው ተጠቅሷል።

ከምልከታው ጎን ለጎን የመንገድ ፕሮጀክቶች የንቅናቄ መድረክ እንደሚካሄድ ታውቋል።

ሚኒስትሯን ጨምሮ ከፌደራልና ከክልል ለመጡ ከፍተኛ አመራሮች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች በአጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም