ቀጥታ፡

የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሠላም ነው-በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች

አዲስ አበባ ፤ ጥር 29/ 2017 (ኢዜአ) :-የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሠላም ነው ሲሉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ።

በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት የሚገልፅ ሰልፍ አካሂደዋል።

ነዋሪዎቹ ለትግራይ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነት አያስፈልግም፣ በክልሉ ያለውን ሠላማዊ እንቅሥቃሴ እና መሠል ሥራዎች በማሥተጓጎል የሚገኝ ጥቅም የለም የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

ለትግራይ እና ነዋሪዎቿ ሠላም በምንም የማይተካ መሆኑንም ሰልፈኞቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በመነጋገር እንዲፈቱ እና ለሠላም ጠንቅ ከመሆን እንዲታቀቡም አስገንዝበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት የትግራይ ክልል ሕዝብ ካለፈው ቁስሉ ሳያገግም አሁንም በጦርነት ስጋት እና ሽብር ላይ መሆኑን ገልፀው በትግራይ ልህቃን መካከል መከፋፈል መኖሩን በማንሳትም ልህቃኑ ልዩነታቸውን በመግባባትና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ መጠቆማቸው ይታወሳል።

የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በቀጣይ በትኩረት ለመስራት ካስቀመጣቸው ስምንት አንኳር ጉዳዮች ዘላቂ እና አዎንታዊ ሰላምን ማረጋገጥ ነው። ፓርቲው ዘላቂው መንገድ የሰላም መንገድ መሆኑን በፅኑ ስለሚያምን የሰላም አማራጮችን በመጠቀም የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ከብልፅግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም