የትግራይ ህዝብ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነትን የሚሸከምበት አቅም የለውም - የትግራይ ተወላጆች - ኢዜአ አማርኛ
የትግራይ ህዝብ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነትን የሚሸከምበት አቅም የለውም - የትግራይ ተወላጆች
አዲስ አበባ ፤ጥር 29 /2017( ኢዜአ )፦የትግራይ ህዝብ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነትን የሚሸከምበት አቅም የለውም ሲሉ የትግራይ ተወላጆች ጠየቁ።
በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ህዝባዊ የሰላም ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሠላም ነው የሚል መልዕክት እያሰሙ ነው።
የትግራይ ህዝብ ልማት እንጂ ጦርነትን የሚሸከምበት አቅም የለውም የሚሉ ድምጽን እያሰሙ ይገኛል።
በተጨማሪ ሰላም ለሰው ልጆች ያለውን ውድ ዋጋ በማስተጋባት ፤ በክልሉ ትምህርት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች በአስተማማኝ ሰላም እንዲካሄዱ ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ልሂቃን ልዩነታቸውን በመግባባትና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲፈቱ ጠየቁ
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በአግባቡ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
ሰልፈኛው የትኛውም ኃይል የትግራይ ህዝብን ዳግም ዋጋ ከሚያስከፍል አካሄድ ራሳውን መቆጠብ እንዳለበት በነቂስ ወጥቶ የሰላም ድምፁን እያሰማ ነው።